አዲስ ነገር – ጥሰት የፈጸሙ የትምህርት ተቋማት

ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱ ተነገረ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 108 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና 147 ካምፓሶች ላይ ሚያዚያ 10 እና 11 ቀን 2014 ዓ.ም ድንገተኛ ፍተሻ መደረጉን የኤፌደሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በነዚሁ ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ በ24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ካምፓሶቻቸው ላይ የፕሮግራም እና የተቋም መዝጋት እርምጃ መወሰዱን ባለስልጣኑ ጨምሮ ገልጿል፡፡
በተጨማሪም በ82 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ቀላል የማስጠንቀቂያ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን በቀጣይ የተገኘባቸውን ክፍተቶች በማስተካከል በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ለባለስልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርጉም ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ሰምተናል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ ቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New