Sports

EBS SPORT – ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ2022 የቫሌንሲያ ማራቶን ልትወዳደር መሆኑ ተዘግቧል

የ5000ሜ.የ10,000እና የግማሽ ማራቶን የአለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው አትሌቷ በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው የኦሎምፒክ መድረክም ሀገሯን በመወከል የነሃስ ሜዳሊያ ማሳካቷ ይታወሳል ፡፡

ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በቫሌንሲያ በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸናፊ በመሆን ክብረወሰኑን በእጇ ያስገባችው አትሌቷ አሁን ደግሞ በዚሁ ስፍራ በታህሳስ ወር በሚደረገው የማራቶን ውድድር እንደምትሳተፍ የአለም አትሌቲክስ አስታውቋል፡፡

ከምርጥ ማራቶኖች መካከል አንዱ እንድሆነ የሚነገርለት የቫሌንሲያ ማራቶን በየጊዜው አዳዲስ ፈጣን ሰዓቶች እንደሚመዘገቡበትም ይታወቃል   ከዚህ ቀደም በ10,000 ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆኑት  ኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያና እና ሆላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን በማራቶን ውድድር ላይ  ተሳትፈው እንደማያዉቁ ይታወቃል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:00 ሰዓት እስከ 7:30 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መረጃዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New