አዲስ ነገር – 400 ሚሊዮን ብር ድጎማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነቱን ለመቅረፍና የተለያዩ ምርቶች ወደ ከተማዋ እንዲገቡ ለማድረግ የ400 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ድጎማ መደበ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ባካሄደው አንደኛ አመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው እስካሁን ድረስ 1 ቢሊዮን ብር መድቦ የተለያዩ ምርቶች ወደ ከተማዋ እንዲገቡ የተደረገ ቢሆንም አሁንም የዘይት አቅርቦት ላይ እጥረት በመኖሩ ተጨማሪ ድጎማ መደረጉን አስታውቋል፡፡
እንዲሁም የውይይት መድረኩ ካጸደቃቸው ሌሎች ተጨማሪ ውሳኔዎችን መካከል መሬትን ፍትሀዊ በሆነ አግባብ ለልማት ለማዋል 89 የሚሆኑ ቦታዎችን ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለቅይጥ አገልግሎት እንዲውል የከተማውን ፕላን ባስጠበቀ አግባብ በግልፅ ጨረታ እንዲቀርቡ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በከተማችን ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በማህበር ተደራጅተው ቤት መገንባት የሚያስችላቸው ደንብ መጽደቁንና አፈፃፀሙም በከተማችን ካለው የቤት አቅርቦት ማዕቀፍ ጋር ተጣጥሞ እንዲሄድም ካቢኔው መወሰኑ ተነግሯል፡፡ መረጃውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የማህበራዊ የትስስር ገጽ ነው ያገኘነው፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New