News

አዲስ ነገር – የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል

ጥበባትና ባህል ለቀጣናዊ ትስስር በሚል መሪ ቃል የተሰናዳዉ የምሥራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ፌስቲቫሉን እንዳሰናዳዉ የሰማን ሲሆን ከሰኔ 7 እስከ 12 /2014 ዓ.ም በተለያዩ መርሃግብሮች እንደሚካሄድ ሰምተናል።
የቀጣናውን ሀገራት ትስስር በማጠናከር በኩል የላቀ ሚና ይኖረዋል የተባለለት ይህ ፌስቲቫል በሚመጡት አመታት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሰራልም ተብሏል።
ፌስቲቫሉ በይፉ መከፈቱ በተነገረበት መርኃግብርም የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዲሁም የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ተወካዮች ታድመዋል።
በፌስቲቫሉ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ተወካዬች የየሀገራቸውን ባህላዊ ሙዚቃዎችና ባህላዊ ውዝዋዜዎች ያቀረቡ ሲሆን ባህላዊ አልባሳት እንዲሁም የቤት ዉስጥ ማስዋቢያ ጌጦች ለታዳሚያን እይታ ቀርቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New