ኢራን እና እስራኤል
የኢራኑ ሀይማኖታዊ መሪ አያቶላ አሊ ሃማኒ የሃማስ ከፍተኛ መሪ የሆኑት ኢስማኤል ሃኒዬ ቴህራን መገደላቸውን ተከትሎ እስራኤል ላይ የአጸፋ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸው ተሰምቷል።
ሃሚኒ ትዕዛዙን ያስተላለፉት የኢራንን መንፈሳዊ ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ከጠሩ በኋላ ነው፡፡
ሟቹ የሃማስ መሪ ኢስማኤል ሃኒዬ ቴህራን ተገኝተው የነበሩት አዲስ በተሾሙት የኢራን ፕሬዚዳንት መሱድ ፔዚሽኪያን በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም እንደነበር ገልፆ የዘገበው ኒው ዮርክ ታይምስ ነው፡፡