InternationalNews

ኢራን የኒውክለር ተቋማቶቿን በመንግስታቱ ድርጅት ለማስፈተሽ ተስማምታለች መባሉን አስተባበለች።

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ባንስ ከስዊዘርላንዱ ድርድር በኋላ ድርድሩ ጥሩ ነው ኢራንም የኒውክሌር ተቋማቶቿን ከዛሬ ጀምሮ ለማስፈተሽ ተስማማለች ቢሉም ኢራን ግን የለም አልተስማማሁም እያለች ነው።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ የኒውክለር ፕሮግራምን በተመለከተ አዲስ የገባሁ ቃል ኪዳን ወይም ግዴታ የለም ብሏል።

ኢራን ይሄን ያለችው አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አንስታላት ቴህራን ነዳጅን በዶላር መሸጥ በጀመረችበት ወቅት ነው።

ኢራን አሁን ማዕቀቡ በመነሳቱ ነዳጅን በዶላር ስትሸጥ በአስርት ዓመታት ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በስዊዘርላንዱ የእሁድ ስብሰባ አሜሪካና ኢራን በስልሳ ቀናት ሙሉ ስምምነት የሚደርሱበት ፍኖተ ካርታ ላይ ከመግባባት መድረሳቸው ተገልጿል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews