ኢትዮጵያን በአፍሪካ ዋንጫው በዳኝነት እየወከለ የሚገኘው ባምላክ ተሰማ

ኢትዮጵያን በአፍሪካ ዋንጫው በዳኝነት እየወከለ የሚገኘው ባምላክ ተሰማ ሴኔጋል እና ጊኒ የሚያደርጉትን የምድብ ሁለት ጨዋታ በዋና አርቢትርነት ይመራል፡፡ በአለም ዋንጫ አፍሪካ ዋንጫ ኦሎምፒክ እና የአፍሪካ የክለቦች ውድድሮች ላይ በብቃት ውድድሮችን መምራት የቻለው የ41 አመቱ የመሀል ዳኛ ዛሬ ሴኔጋል እና ጊኒ በአፍሪካ ዋንጫው የሚያደርጉትን ወሳኝ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ከደቂቃዎች በኅላ ይመራል፡፡ ባለፉት አስርት አመታት በአለም አቀፋዊ ውድድሮች የሀገሩን ስም ያስጠራው ባምላክ ተሰማ ከመሀል ዳኝነት በተጨማሪ ባሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ግብፅ እና ናይጄሪያ ባደረጉት ጨዋታ በቪዲዮ አሲስታንት ሪፈሪ ላይ መሳተፉ ይታወሳል፡፡

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision

#ኢቢኤስ#EBS