ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በስኬት ማጠናቀቋ ተገለጸ፡፡

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የታላቁ #ሕዳሴ_ግድብ የውሃ ሙሌት በስኬት ማጠናቀቋ ተገልጿል፡፡ ዛሬ ሀምሌ 12/ 2012 ዓም የሁለተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት ተገባዶ በግድቡ አናት ላይ መፈሰስ መጀመሩን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ናቸው ያስታወቁት። ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው በዘንድሮው አመት እየዘነበ ያለው ውሃ መጠን እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ይህም ለሙሌቱ አግዞናል ብለዋል።