ኢትዮጵያ በብሪክስ
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነትን እንድትቀላቀል ከተጋበዘች በኋዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገራቱ ባደረጉት የጥምር ውይይት ላይ ተሳትፊ ሆናለች።
በዓለማችን በፈጣን እድገት ላይ የሚገኙ አምስት አገራት ጥምረት የሆነውና በቅርቡም ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገራትን አዲስ አባል ሊያደርግ የወሰነው ብሪክስ በጋዛ በንጹሀን ዜጎች ላይ እየደረሰ ነው ባለው ሞትና የጦር መሳሪያ ድብደባ ዙሪያ መክሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና፣ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ጨምሮ የሁሉም አባል ሀገራት መሪዎች በበይነመረብ ተገናኝተው በመከሩበት በዚህ ስብሰባ ላይ በጋዛ በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚደርሰው ሞት እንዲበቃና ለተጎጂዎች አስፈላጊው የሰብአዊ ድጋፍ እንዲቀርብ ጥሪ ቀርቧል።