EthiopiaNews

ኢትዮ ቴሌኮምና ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ

ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ አራተኛው ኩባንያ ሆኖ መመዝገቡ ተገለጸ።

ተቋሙ በዚህ ገበያ ላይ መመዝገቡን ይፋ ያደረገው ከኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ጋር በመተባበር በሰጠው የጋራ መግለጫ ነው።

የኢትዮ ቴሌኮም ባለአክሲዮኖች በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ላይ አክሲዮናቸውን ማንቀሳቀስ የሚያስችላቸው ዝግጅት ማጠናቀቁንም ነው በሰጠው መግለጫ ያስታወቀው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ መድረክ ላይ ከመመዝገቡ አስቀድሞ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖቹን ለሽያጭ ገበያ አውጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዚህም መሠረት አጠቃላይ አክሲዮን ከገዙ 47ሺህ 377 ዜጎች ውስጥ 45ሺህ 366 የሚሆኑት የባለቤትነት ማረጋገጫና አክሲዮኖችን ወደ ዲጂታል የመቀየር ሂደታቸውን ሙሉ በሙሉ አጠናቀዋል ተብሏል።

ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖቻቸውን ተፈጻሚነት ባላቸው ህጎች መሠረት የመሸጥ፣ የመግዛት እንዲሁም የማስተላለፍ መብት እንደሚያገኙም ነው ተቋሙ ያስታወቀው፡፡

እስካሁን በሀገሪቱ የመጀመሪያውና ብቸኛው የተደራጀ የካፒታል ማርኬት የሆነው እና በመንግሥትና በግል አጋርነት የተመሠረተው የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ላይ በይፋ ተመዝግበው ተሳታፊ የሆኑ ሦስት የፋይናንስ ተቋማት ብቻ ነበሩ።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv