ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማእከል ስራ አስጀምሯል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ለጥገና የማወጣውን ወጪ እስከ 35 በመቶ ይቀንስልኛል ያለውን ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማእከል ስራ አስጀምሯል፡፡ማዕከሉ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ለተባለው የግልና የመንግስት ተቋማት የመረጃ ክምችትና ስርጭት ጥራቱን የጠበቀ የመረጃ ማእከል የሚሆንና የተለያዩ የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎት መስጠት የሚፈልጉ ድርጅቶችም በአጭር ጊዜ መረጃን በማግኘት ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ የሚያስችል ነው ተብሎለታል፡፡በተጨማሪም በከፍተኛ ደረጃ የሃይል ፍጆታን የሚቀንስ፣ በቀላሉ ፍላጎትን ተከትሎ ሊስፋፋ የሚችልና ፈጣን የሲስተም ተከላ ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ኩባንያው በቅርቡ ያስተዋወቀው ቴሌብር የተሰኘው አገልግሎትም በዚሁ ማእከል ምክንያት የተቀላጠፈ አገልግሎት ይሰጣል ነው የተባለው። በቀጣይም መሰል ማእከላትን በተለያዩ አካባቢዎች ለመገንባት እንደታቀደም ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።