LatestNews

በእስራኤልና የፍልስጤሙ ሀማስ ታጣቂ ቡድን መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርሷል፡፡

በእስራኤልና የፍልስጤሙ ሀማስ ታጣቂ ቡድን መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርሷል፡፡ዛሬ አርብ ማለዳ ላይ የተኩስ አቁሙ ስምምነት የተደረሰው ለአስራ አንድ ቀናት በተካሄደው ወታደራዊ ፍልሚያ በትንሹ 2 መቶ 40 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው፡፡ ከሟቾቹ አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የጋዛ ነዋሪዎች መሆናቸውን ተገልጿል፡፡ የተኩስ አቁሙ እንደተተገበረ አያሌ ፍልስጤማዊያን አደባባይ ወጥተው የታዩ ሲሆን ሀማስ ግን ተኩስ አቁም ቢደረግም ከጠመንጃ ቃታ ሳያነሳ ሁኔታዎችን በቅርብ እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል፡፡ከ11 ቀናት የአየርና የሚሳኤል ድብደባ በኋላ እስራኤልም ሆነች ፍልስጤማዊያኑ በየፊናቸው ድሉ የኔ ነው እያሉ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል፡፡የተኩስ አቁሙ እንዲደረግ የሽምግልና ሚናውን የተጫወቱት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተኩስ አቁሙ አንዳች መልካም ነገር እንደሚያመጣ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡ትናንት ሀሙስ ብቻ እስራኤል ከአንድ መቶ በላይ የአየር ጥቃት ፈጽማ የጋዛን መሰረተ ልማቶች ያፈረሰች ሲሆን ሀማስም የብቀላ እርምጃ ወስዷል፡፡