LatestNews

ባለፉት 20 አመታት ውስጥ ሙስናን ለመከላከል በሰራሁት ስራ ከ2 ነጥብ 4 ቢልዮን ብር በላይ የሚሆን የአገር ሃብት ከስርቆት አድኛለሁ ሲል የፌደራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

#ባለፉት 20 አመታት ውስጥ ሙስናን ለመከላከል በሰራሁት ስራ ከ2 ነጥብ 4 ቢልዮን ብር በላይ የሚሆን የአገር ሃብት ከስርቆት አድኛለሁ ሲል የፌደራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን 20ኛ አመት ያከበረ ሲሆን ከሁሉም ክልሎች በጥያቄና መልስ ውድድር ያሸነፉ ተማሪዎችንና በስነ ምግባራቸው የተመሰገኑ በስራቸውም የታመኑ አካላትን የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ሸልሟል፡፡ 229 ተማሪዎች የተሸለሙበት የስነምግባርና ጸረ ሙስና ጥያቄና መልስ ውድድር የ9ነኛና የ11ኛ ክፍል እንዲሁም የግልና የመንግስት የኮሌጅና የዩንቨርሲቲ ተማሪዎችን ያሳተፈ ሲሆን የሴትም የወንድም ተሸላሚዎች ቁጥር እኩል እንደሆነ ተገልጿል::በክልል ደረጃም የሲዳማ የደቡብና የኦሮሚያ ክልሎች ባሳዩት የሙስና መከላከል ስራ የተሸለሙ ሲሆን በግል እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት እያገለገሉ ያሉና አርአያ ናቸው የተባሉ 286 ግለሰቦችም የሽልማቱ አካል ናቸው፡፡ በግንቦት 16/1993 የተቋቋመው የፌዴራል የስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በዕለቱ በሙስና መከላከል ረገድ በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን የገለጸ ሲሆን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ በገባው የሃብት ማስመዝገብ ተግባርም በአገር አቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 8 ሚልዮን የሚሆኑ በየደረጃው ያሉ ሃላፊዎች ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ አድርጌአለው ብሏል፡፡