EthiopiaNews

እንግሊዝ የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ዘርፍ ደኅንነት ለማዘመን የሚያስችል የቴክኖሎጂ ድጋፍ አደረገች።

የእንግሊዝ መንግሥት የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ዘርፍ ደኅንነት ለማዘመን የሚያስችልና በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላይ የሚውል የቴክኖሎጂ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልች የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሲሳይ ቶላና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አስረክበዋል፡፡

ዳይሬክተር ጀነራሉ ሲሳይ ቶላ ድጋፉ አገራቱ በጋራ ደኅንነት ላይ ያላቸውን ዘላቂ አጋርነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰው ተለዋዋጭ የሆነውን የአቪዬሽን ደኅንነት ስጋት አስቀድሞ በመከላከል የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ የበላይነት ለማስጠበቅ የሚያስችል መሂኑን ገልጸዋል፡፡

በተለይም ኢትዮጵያ በዓመት 120 ሚሊዮን መንገደኞችን የሚያስተናግድ ግዙፍ አየር ማረፊያ በቢሾፍቱ እየገነባች ባለችበትና በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2027 የኮፕ-32 ጉባኤን ለማስተናገድ በምትዘጋጅበት ወቅት ከፍተኛ የአቪዬሽን ደኅንነት ዝግጁነት ስለሚጠይቅ መሰል ትብብሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልች በበኩላቸው የሁለቱን አገራት የቆየ ወዳጅነት በማስታወስ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቁልፍ የዓለም ተጓዦች ማዕከል በመሆኑ ደኅንነትን የማረጋገጥ ጉዳይ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አብራርተዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews