EthiopiaNews

እውን የጥቁር ገበያ ዋጋ ቀንሶ ይሆን??

በዛሬው እለት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን የዲጅታል ቡድን የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል ሲል በብሔራዊ እና አምባሳደር አካባቢ ቅኝት አድርጓል።

በዚሁ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ከሁለት ቀናት በፊት አንዱን የአሜሪካ ዶላር በትይዩ ገበያው ወይም ብላክ ማርኬት በሚባለው በ125 ብር ሲገዙ እንደነበር ገልፀው ከትላንት ጀምሮ ግን አንዱን የአሜሪካ ዶላር በ115 ብር እንደሚገዙ ለማወቅ ችለናል። በዚህም በ10 ብር ማሽቆልቆሉን ነግረውናል።