ከሬሚታንስ የሚገኘው ገቢ
በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው የሚልኩት ገንዘብ ወይም ሬሚታንስ አሁን ላይ ሀገሪቱ ከውጭ እርዳታና ከቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ከምታገኘው ገቢ እንደሚበልጥ ተገለጸ።
የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በትናንትናው ዕለት ይፋ ባደረገው የ2026 የዓለም የስደት ሪፖርት ኢትዮጵያ በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ስደተኞች የምታገኘው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ትልቅ መሆኑን አንስቷል።
በፈረንጆቹ 2024 ብቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስደት ላይ የሚገኙ ዜጎች ወደ ሀገራቸው የላኩት ገንዘብ ከ900 ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን የጠቀሰው ሪፖርቱ ከዚህም ውስጥ ከፍተኛው ድርሻ ወደ ኢትዮጵያና መሰል በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የተላከ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡
ይህም የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የስደተኞች ድርጅቱ ያወጣው መረጃ ጠቁሟል።
ድርጅቱ በሪፖርቱ ለስደት ህጋዊ መንገዶች መጥበባቸው ስደትን እንደማያስቆም ገልጾ ይልቁንም ሕጋዊ የጉዞ መንገዶች ሲጠቡ ዜጎች አደገኛና ኢ-መደበኛ መንገዶችን ለመጠቀም እንደሚገደዱ ገልጿል።
ሪፖርቱ በማጠቃለያው የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎች ገንዘብ ወደ ሀገራቸው የሚልኩበትን የአገልግሎት ክፍያ እንዲቀንስና ለወጣቶች ሕጋዊ የሥራ ስምሪት እድሎችን እንዲያሰፋም ጥሪ አቅርቧል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
