EthiopiaNews

‎ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎች

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1 ሺህ 400 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
‎
ከተመላሾች መካከል ከ800 በላይ ወንዶች፣ ከ600 በላይ ሴቶችና 76 ጨቅላ ህፃናት የሚገኙበት ሲሆን ከ80 በላይ ያህሉ ደግሞ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል።
‎
መስከረም 5 ቀን 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ64 ሺህ 300 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለሳቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
‎
‎ሚኒስቴሩ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማበረታታት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነም ተጠቁሟል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN