ከቬኑዙዌላ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በኋላ የነፍስ አድን ሥራው ሲቀጥል፤ ሁለት የአስራ አንድ ዓመት ሕፃናትን በሕይወት ማግኘት ተችሏል።
የአገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ እንዳሉት በሳምንቱ መጨረሻ 33 ሰዎችን በሕይወት ማዳን ሲቻል ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ሕፃናት በተለያዩ ሕንፃዎች ነገር ግን በተከታታይ በሕይወት ሊገኙ ችለዋል።
ይሁንና አሁንም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተጎጂዎችን ነፍስ ለማዳን ጥረት እየተደረገ ነው።
በአንዳንድ ሕንፃ ፍርስራሽ ስር የሰዎች ድምፅ እየተሰማ ሲሆን ነገር ግን ፍርስራሽ ግድግዳዎችን ለማንሳት ከባባድ የግንባታ ማሽነሪዎች አስፈልገዋል።
ሰዎችን በሕይወት የማግኘት ዕድል ሊኖር የሚችለውም በፍርስራሽ ስር ውሃና ምግብ ካገኙ ብቻ ነው እየተባለ ነው። በቬኑዙዌላ በሰከንዶች ልዩነት ሁለት ከባድ ርዕደ መሬቶች የደረሱት ባለፈው ረቡዕ ነበር።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
