EthiopiaNews

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የህፃን ሄቨንን እናት አገኟት! እናስ ምን አደረጉ?

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልጇን በግፍ ለተነጠቀችው ህፃን ሄቨን እናት መኖሪያ ቤት መስጠቱን አስታውቋል።

የፍትህ ሂደቱን በቅርበት ለመከታተል፣ እናትየው ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆን እና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲሁም ተበዳይ ግለሰቧ በሙያዋ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንድትሰራ ማመቻቸቱን ከንቲባ አዳነች አበቤ ተናግረዋል።
ድርጊቱ ተገቢውን ፍትህ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናትን ተጋላጭነት ለመቀነስ አስተዋፅዖ አለው ያሉት ከንቲባዋ የዚህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንወጣ ብለዋል።