EthiopiaLatestNews

ከአንዲት እናት 28 ኪሎ ግራም እጢ ከሆዳቸው መውጣቱ ተሰማ

በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ በሚገኘው ሰላም ሆስፒታል ከአንዲት እናት 28 ኪሎ ግራም እጢ ከሆዳቸው መውጣቱ ተሰማ ።ከምዕራብ ጉጂ ዞን ሃሚባላ ዋማና ወረዳ ጮርሶ ጎሊጃ ቀበሌ በመምጣት በሰላም ሆስፒታል የህክምና ክትትል ሲያደረጉ የቆዩት የ48 አመት እናት ከሆኑት ወ/ሮ አበሩ አላኮ በተደረገላቸው የቀዶ ጥገና ህክምና 28 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ ከሆዷ መዉጣቱን የማህጸንና ጽንስ ኢስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ጌታቸዉ መርጊያ ገልጸዋል ቀዶ ጥገናው 3 ሰዓታት የወሰደ መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር ጌታቸዉ በአሁኑ ሰዓት ወ/ሮ አበሩ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ መግለጻቸውን የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል ።

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision