ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ ገለጸ።
ፖሊስ አክሎም አደጋው የተከሰተው በደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል ልዩ ስሙ ሐረጎ በሚባለው አካባቢ መሆኑ ገልጿል።
ዛሬ ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ማለዳ ላይ ሲጓዝ የነበረው ይህ አውቶቡስ መንገድ ስቶ በግምት 100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል በመግባቱ የተነሳ የ28 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሊያልፍ ችሏል ተብሏል።
በተጨማሪም በጉዞው ላይ በነበሩ ሌሎች በርካታ ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው የተባለው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
