ከዳታ ማይኒንግ 25 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ
በኢትዮጵያ በዳታ ማይኒንግ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው ከሚገኙ ዘጠኝ ድርጅቶች በበጀት ዓመቱ ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
ተቋሙ ከዘርፉ 27 ነጥብ 71 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መሰብሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም እቅዱን ማሳካት ያልቻለው ድርጅቶቹ በጠየቁት የኃይል ፍላጎት መሠረት በቂ ኃይል ማቅረብ ባለመቻሉ በዕቅዱና በአፈፃፀሙ መካከል ክፍተት መስተዋሉን ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልጿል።