EthiopiaNews

ከገቢ ግብር ነጻ የሆኑ ግብዓቶች

በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ ተሰማርተው ግብአቶችንና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ መፈቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

አስመጪዎች ግብቶችንና ምርቶችን ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ ወደ አገር አስገብተው ለግብአቱ ወይም ለምርቱ ገበያ ባገኙ ጊዜ ቀረጥና ታክሱን የሚከፍሉበትን አሰራር የሚፈቅድ የነጻ የንግድ ቀጠና አሰራር መዘርጋቱን ያስታወሰው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን ስርዓት የሚያስፈጽሙ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች በየአካባቢው መቋቋማቸውንም ጠቁሟል፡፡

እነዚህ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች ባለሃብቶችን የበለጠ የሚሰቡ እንዲሆኑ ለማድረግ ይሄንን አስራር መዘርጋቱን የጠቀሰው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለሃብቶች ይህንን እድል በመጠቀም በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ እንዲሰማሩም ጥሪ አቅርቧል፡፡

መረጃው ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN