ከአትሌታችን ጎተይቶም አንደበት…!

ከአትሌታችን ጎቲይቶም አንደበት…! ለቤተሰቤ 3ኛ ልጅ ነኝ። እናቴ እኔን አርግዛ በአካባቢው ትልቅ ክብር ታገኝ ነበር፣ ከዚያ ስወለድ “ጎቲይቶም” አለችኝ – ‘እመቤት’ እንደማለት። ደስ ብሎኛል፣ ደስታዬ ግን የተዘበራረቀ ነው።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደተደሰተው የእኔ እናትና አባትም ሲደሰቱ ብሰማና ባያቸው ደስ ይለኝ ነበር። እግዚአብሔር ሰላሙን ያምጣና … ። ደስታው ትልቅ ነው፣ ግን ደግሞ ትንሽ ተዘበራረቀብኝ።

” አምና በዚህ ጊዜ የት እንደነበርኩ አውቃለሁ። መንገድ ተከፍቶ ነው የወጣሁት። በመጀመርያ እግዚአብሔር ነው የረዳኝ፣ ከዚያም በማሰልጠን ብቻ ሳይሆን እንደ ወንድም ሆነው እንዳይከፋኝ እያገዙ ለዚህ ያበቁኝ አሰልጣኞቼ ናቸው። አይዞሽ ሁሉም ያልፋል እያሉ እዚህ አደረሱኝ። አመሰግናቸዋለሁ!

ምንጭ : አብይ ወንዲፍራው አሪገን አሜሪካ