ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ለአፍሪካ
ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ቻይና ለአፍሪካ አገራት እንደምታደርግ ፕሬዝዳንት ሺ ዢ ፒንግ ከ50 በላይ የአፍሪቃ አገራት መሪዎች በተገኙበት 9ኛው የአፍሪካ ቻይና ጉባዬ ላይ መናገራቸው ተሰምቷል።
ፕሬዝዳንቱ በደረጉት የጉባኤው የመክፈቻ ንግግራቸው የገንዘብ ድጋፉ ስምምነቱ በዋናነት ለሥራ እድል ፈጠራ፣ ለኢንዱስትሪ፣ ግብርና፣ ኢንቨስትመንት፣ ለንግድ እና መሰል ዘርፎች እንደሚውል አስታውቀዋል።
ድጋፉ በቀጣይ ሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ይደርጋል መባሉን ጨምሮ የዘገበው ፍራንስ 24 ነው፡፡