ወደ ኢትዮጵያ እስከ ገና ዋዜማ ድረስ የሚደረጉ በረራዎች መሙላት

ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እስከ ገና ዋዜማ ድረስ የሚደረጉ በረራዎች መሙላታቸውን የዲያስፖራ ኤጀንሲ ዛሬ ለአዲስ ነገር አሰታውቋል።የኤጀንሲው ም/ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር መሃመድ እንድሪስ እንደገለፁት ከታቀደው አላማ አንጻር እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት ከግማሽ በላይ የሚሆነው ተሳክቷል ማለት እንደሚቻል ጠቁመው የቪዛ ጋር የተያያዙ ችግሮች እልባት እንደተሰጣቸውም ተናግረዋል፡፡ጥሪውን ተከትለው ወደ አገር የሚገቡ ዳያስፖራዎችን ለማስተናገድ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራና ዳያስፖራ ኤጀንሲ የሚያስተባብር ኮሚቴ እንደተሰየመ የተነገሩ ሲሆን ከኤርፖርት አቀባባል ጀምሮ ጉዳት የደረሰባቸውን ቦታዎችን ማስጎብኘት ድረስ የሚያስተባብሩ 6 ንኡሳን ኮሚቴዎች እንደተደራጁም ተጠቁሟል፡፡ዘገባው የሃና ኣብዳታ ነው።

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision#ኢቢኤስ#EBS