InternationalLatestNews

ዓለም አቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት መከበር ተጀመረ::

ዓለም አቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት መከበር ተጀመረ የጤና ሚኒስቴር ጡት የማጥባት ሳምንትን በተመለከተ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ህጻናትን ጡት ማጥባት ዘርፈ በዙ ጥቅም እንዳለዉ አስታዉቋል። ለአካላዊና ለአዕምሯዊ እድገታቸው ለበሽታ መከላከል አቅማቸው እና ለእድሜ ልክ ጤናቸው የጎላ ፋይዳ እንዳለዉም ተጠቁሟል።፡፡ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በሀገራችን ጡት የሚያጠቡ እናቶች 97 በመቶ እንደሆነ ገልጸዉ በተገቢው መንገድ የማጥባት ልማድ ላይ ክፍተት እንዳለዉ ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ጡት የማጥባት ሃላፊነት ከእናቶች ባለፈ የሁሉም ሃላፊነት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል። እናቶች ጡት የሚያጠቡበትን ስፍራ አመቺ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ ካሳለፍነው እሁድ ሃምሌ 25/2013 ዓ.ም እስከ ነሃሴ 1/2013 ዓ.ም ድረስ ጡት ማጥባትን መጠበቅ የጋራ ሃላፊነት በሚል መሪ ቃል የሚከበር ይሆናል።