EthiopiaNews

የህግ ትርጉም

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት በአንድ ባለይዞታ ሊመዘገብ የሚገባን የከተማ ይዞታ ከአንድ በላይ የሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ለተለያዩ ሰዎች ተደርቦ ቢሰጥ ለቦታው ባለመብትነት በተመለከተ ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረውን የሕግ ትርጉም በመለወጥ አዲስ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም መሠረት የይዞታ ማረጋገጫ ወይም ካርታ ለተለያዩ ሰዎች ተደርቦ ተሰጥቶ ሲገኝ ለቦታው ባለመብትነት ቅድሚያ የሚሰጠው መጀመሪያ ላስመዘገበው ሰው ነው በሚል ተተርጉሟል፡፡

ይህ አዲስ ውሳኔ መጀመሪያ ካርታ ከወሰደው ይልቅ ንብረት አፍርቶ ያለው ባለመብት ሊሆን ይገባል የሚለውን አስገዳጅ ትርጉም የሻረ ሲሆን ከመጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩም ነው የተነገረው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv