የሕፃን ኖላዊት ዘገየ ግድያ
በጎንደር ከተማ ኖላዊት ዘገየ የተባለች የሁለት ዓመት ህጻን በአጋቾች ታግታ ከቆየች በኃላ ቤተሰቦቿ እንዲከፍሉ የተጠየቁትን ገንዘብ ዘግይታችሁ ነው የከፈላችሁት በማለት ህጻኗን ገድለው በቤተሰቦቿ ደጅ ጥለዋት መገኘቱን አሚኮ ከቤተሰቦቿ አገኘሁት ባለው መረጃ ገልጿል፡፡
በጎንደር ከተማ በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዜጎችን አግቶ ገንዘብ መጠየቅ የተለመደ ህገወጥ ተግባር መሆኑም ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
ጣቢያችን ኢቢኤስ ቴሌቭዥን በህጻን ኖላዊት ዘገየ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ በጉዳዩ ዙርያ ዝርዝር ዘገባ ይዘን እንደምንመለስ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡