የመደራጀት ነጻነት ጉዳይ
በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚተላለፉ እገዳዎች በመደራጀት ነጻነትና በሲቪል ምኅዳሩ ላይ የፈጠሩት አሉታዊ ተጽዕኖ አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ ተገለጸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የመደራጀት ነጻነትን አስመልክቶ ባካሄደው የባለድርሻ አካላት ውይይት ላይ ሲሆን በመድረኩም ሠራተኞች ስለመደራጀት መብት ያላቸው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆን ተደራጅተው መብቶቻቸውን እንዳይጠይቁ እክል መፍጠሩ፤ መብታቸውን በሚጠይቁ ሠራተኞች ላይ ከሥራ ማባረር ጀምሮ የተለያዩ አስተዳደራዊ ጫናዎች የሚደርሱባቸው መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች የመደራጀት ነጻነት በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ጥበቃ ከተደረገላቸው መሠረታዊ መብቶች መካከል አንዱ መሆኑንና ማንኛውም ሰው ሕጋዊ ለሆነ ማንኛውም ዓላማ በማኅበር የመደራጀት መብት እንዳለው የተደነገገ በመሆኑ ለተፈጻሚነቱ ምቹ የሕግና የአሠራር ማዕቀፎችን መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
