የማዕድን ማምረትና ምርምር ፈቃድ ተሰጥቷቸው የነበሩ 63 ተቋማት ፈቃድ ተሰረዘ::

63ቱ ተቋማት ፈቃዳቸው የተሰረዘው ተቋማት በአፈፃፀም ድክመት፣ የህዝብና መንግስት ሃብትን በማባከናቸው እንዲሁም በወቅቱ ፈቃድ ባለማደሳቸው፣ ከአቅም በታች በማምረትና የሮያሊቲ ክፍያ ባለመፈፀማቸው መሆኑን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል።

ፈቃዳቸው ከተሰረዘባቸው 63 ተቋማት መካከል 38ቱ በማዕድን ማምረት ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩ ሲሆኑ 25ቱ ደግሞ በማዕድን ምርምር ላይ የተሰማሩ መሆናቸውንም ሚኒስትሩ መግለጻቸው ኢዜአ ዘግቧል።#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs