EthiopiaLatestNews

በዛሬ ዕለት ከኬንያው አቻቸው ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን የሞያሌ የጋራ ፍተሻ ኬላና ጎዳናን የመረቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአጎራባች አካባቢ ነዋሪዎች በትብብር ጉዳይ ላይ እንዲሰሩ መክረዋል።

ሁለቱ መሪዎች በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ እንዳሉት በድንበሩ ላይ ያሉት ሕዝቦች ከሦስት ትውልድ በላይ በመከባበር አርዓያነት ያለው ጉርብትናን መስርተዋል ያሉ ሲሆን ይህም የሁለቱ ሀገራት መንግሥታት በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ ግንኙነት እንዲኖራቸው ሚና ተጫውቷል ብለዋል።

ወጪና ገቢ ምርቶችን በማንሳቱ ሂደት ይጠፋ የነበረውን ጊዜና ገንዘብ ይቆጥባል በተባለለት አዲሱ የጋራ ፍተሻ ኬላና ጎዳና ምርቃት ላይ መሪዎቹ በየተራ ባደረጉት ንግግር ላይ ጠ/ሚ ዐቢይ ለሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች በእኩልነት ላይ የተመሰረተ እድገት ሲባል ድንበር ተሻጋሪ ግንኙነቱን ተቋማዊ ቅርፅ ልናሲዝ ይገባል ብለዋል፡፡

የኬንያው መሪ ኡሁሩ ኬንያታም እንዲሁ የድንበር ከተማዋ ሞያሌ እንደ መካከለኛው ምስራቋ ዱባይ ትልቅ የንግድ ማዕከል እንድትሆን ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡ ንግዱ ላይ ያሉ ከታሪፍ ውጭ ያሉ እንቅፋቶች ሊወገዱ ይገባልም ነው ያሉት፡፡#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs