EthiopiaNews

የምርጫ ቦርድ ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ሕጉ መሠረት የምርጫው ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስ መራጮች በትዕግሥት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቀረበ።

ቦርዱ ትናንት በተደረገው ምርጫ ድምፅ የሰጡ መራጮችን እንደሚያመሰግን ገልጾ የምርጫው ውጤት በቦርዱ ይፋ እስኪደረግ ድረስ መራጮች በትእግስት እንዲጠባበቁ ነው ጥሪውን ያቀረበው።

መራጮች ከሌሎች ከማንኛውም ምንጮች የሚወጡ መረጃዎችን ከማሠራጨት እንዲቆጠቡ ቦርዱ አሳስቧል፡፡

ቦርዱ ትናንት በተጠናቀቀው የድምፅ አሰጣጥ 40 ሚሊየን የሚጠጉ መራጮች ድምፅ መስጠታቸውን መግለፁ ይታወሳል።መረጃው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv