EthiopiaNews

የምርጫ ጊዜያዊ ውጤት

በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የሰባተኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ መደረግ ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመላው ሀገሪቱ የ7ኛው ብሔራዊ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በይፋ ከለሊቱ ሰባት ሰአት ገደማ መጠናቀቁን ያስታወቀ ሲሆን የድምጽ ቆጠራው መካሄድ መቀጠሉንም ጠቅሷል፡፡

በዚህም የድምጽ ቆጠራው የተጠናቀቀባቸው የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት ይፋ እያደረጉ እንደሚገኙም ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች ካሰማራቸው ሪፖርተሮች ማረጋገጥ ችሏል፡፡

የድምጽ ቆጠራው እና ጊዜያዊ ውጤት የመለጠፍ ተግባራት አሁንም መቀጠሉ ተጠቁሟል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv