የምግብ ዋጋ ንረት
የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ፣ የአለም ባንክ እና የአለም የምግብ ፕሮግራም በኢራን ጦርነት ምክንያት የተከሰተው የነዳጅ እና የማዳበሪያ ዋጋ ጭማሪ የምግብ ዋጋ ንረት እንዲባባስ ሊያደርግ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ተቋማቱ በጋራ ባወጡት መግለጫ በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የነዳጅ እና የማዳበሪያ ዋጋ ጭማሪ ስጋት መፍጠሩን ገልጸው፤ ይህም በተለይ ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ እና ሸቀጦችን ከውጭ የሚያስገቡ ሀገራት በእጅጉ ተጎጂ ይሆናሉ ነው ያሉት፡፡
በምግብ ዋጋ ግሽበቱ በተለይ ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ እና ሸቀጦችን ከውጭ የሚያስገቡ ሀገራት በእጅጉ ተጎጂ ይሆናሉ ተብሏል።
የኢራን ጦርነት የአለም አቀፉን የነዳጅ ገበያ ሰንሰለት በእጅጉ ማስተጓጎሉን የጠቀሱት ተቋማቱ የነዳጅ ዘይት፣ የናፍጣ እና የማዳበሪያ ዋጋ ጭማሪ ከትራንስፖርት መስተጓጎል ጋር ተያይዞ የምግብ ዋጋ ንረቱን ያባብሳል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአለም የምግብ ፕሮግራም በበኩሉ ይሄው የኢራን ጦርነት እስከ ሰኔ ወር የሚቀጥል ከሆነ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ ሊጋለጡ ይችላሉ ሲል ማስጠንቀቁ የሚታወስ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews