የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኙ የቦብ ማርሌ ልጅን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ሙዚቀኞች የሚሳተፉበት ኮንሰርት ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኙ የቦብ ማርሌ ልጅ ጁሊያን ማርሌን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ሙዚቀኞች የሚሳተፉበት ኮንሰርት ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

እንግሊዛዊ ጀማይካዊ ዜግነት ያለውና ሁለት ጊዜ ለግራሚ እጩ ሆኖ የቀረበው ጁልያን ማርሌ በኢትዮጵያ ለሚያደርገው ኮንሰርቱም ትላንት ማምሻውን ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል።

ላለፊት 18 ዓመታት ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ የተለያዮ ስራዎችን ሲያከናውን የነበረው አይዞን ፋውንዴሽን ቱር ኤንድ ፕሮመሽን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በዚህ ኮንሰርት ላይ ከጁሊያን ማርሌ ውጪ ሌሎች የውጭ ሀገርና የሀገር ውስጥ ሙዚቀኞች ይሳተፉበታል ተብሏል።

በጊዮን ሆቴል በሚሰናዳው በዚህ ኮንሰርት ላይ መታደም የሚፈልጉ ሁሉ የመግቢያ ትኬቱን በዳሽን ባንክ በኩል ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

ትኬቱን ከኮንሰርቱ አስቀድመው ለሚገዙ መደበኛው ዋጋው 600 ብር ቪአይፒ ደግሞ 1200 ብር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በእለቱ በር ላይ የሚሸጠው የትኬት ዋጋም እንዲሁ መደበኛ 800 ብር ቪአይፒ 1500 ብር መሆኑን ሰምተናል።

Join Our Telegram

Click Here To follow Us