InternationalNews

የሱዳን የጎርፍ አደጋ

በሱዳን በጣለው ከባድ ዝናብ 32 ሰዎች መሞታቸውን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ እንዳለው በሱዳን 7 ግዛቶች በጣለው ከፍተኛ ዝናብ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 107 ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን 5 ሺህ 575 ቤቶችን ማውደሙን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።