የባለስልጣን መ/ቤቱ ፈቃድ
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለፕራይም ካፒታል አ.ማ. የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ሰጥቷል።
በዚህም ድርጅቱ ከባንክ ቡድን ውጭ በሆነ የኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ እንዲሠራ ፈቃድ ተሰጥቶቷል።
ባለስልጣኑ ለፕራይም ካፒታል አ.ማ. አራት ተሿሚ እንደራሴዎችም ፈቃድ የሰጠ ሲሆን የዘጠኝ የቦርድ አባላት ሹመትንም አጽድቋል።
በኢትዮጵያ የተፈቀደላቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ጠቅላላ ቁጥር ወደ አስራ ሰባት እንዲሁም የኢንቨስትመንት ባንኮችን ቁጥር ወደ ስድስት መድረሱ ተገልጿል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ የኢንቨስትመንት ባንኮች የካፒታል ገበያ ግብይቶችን በማሳለጥ እና ኢንቨስተሮች በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ በማድረግ፤ በካፒታል ገበያ ልማት እና በኢንቨስተሮች ጥበቃ ረገድ ያላቸውን ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል።
መረጃው ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
