የባንኩ ድጋፍ ለአፍሪካ
አፍሪ ኤግዚም ባንክ በኢራን ጦርነት ምክንያት በአፍሪካ እና ካሪቢያን ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቋቋም የሚያስችል የ10 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ።
ባንኩ “ገልፍ ክራይሲስ ሪስፖንስ ፕሮግራም” በሚል ያጸደቀው የድጋፍ ፕሮግራም በዓለም አቀፍ ንግድ በተለይም የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ያስከተለውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቀልበስ ያለመ መሆኑን ገልጿል።
መሰረታዊ ሸቀጦች በተለይም ነዳጅ፣ ጋዝ፣ የምግብ አቅርቦት፣ ማዳበሪያ እና መድኃኒት ያሉ አስፈላጊ ምርቶች አቅርቦት እንዳይቋረጥ የአጭር ጊዜ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የፕሮግራሙ ዋነኛው ትኩረት እንደሆነ ተገልጿል።
የባንኩ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኤሎምቢ (ዶ/ር) ድጋፉ የአፍሪካ ሀገራት አሁን ያለውን ቀውስ በሰላም እንዲሻገሩና በቀጣይ ለሚከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎች ዝግጁ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል ብለዋል።
መረጃው ከአፍሪ ኤግዚም ባንክ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews