የቤኔሉክስ ቢዝነስ ፎረም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ – የቤኔሉክስ ቢዝነስ ፎረም ዛሬ በሉክሰምበርግ በይፋ መከፈቱን አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ፎረሙ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች፣ ባለሀብቶች፣ የንግድ ምክር ቤቶች እና የልማት አጋሮችን በማገናኘት የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልጿል።
ፎረሙ በኢትዮጵያ እና በቤኔሉክስ ሀገራት መካከል አዳዲስ የቢዝነስ እድሎችን ፈትሾ ለጋራ ተጠቃሚነት ለመስራት ጉልህ ሚና ያለው መድረክ ነው ተብሏል።
በቢዝነስ ፎረሙ ከ20 በላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች በመሳተፍ በኢትዮጵያ ቁልፍ የልማት ዘርፎች እያደገ ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጭ እያሳዩ ነው ተብሏል።
የሉክሰምበርግ እና የቤኔሉክስ ባለሀብቶች እያደጉ ያሉትን እድሎች ተጠቅመው ከኢትዮጵያ ጋር የረዥም ጊዜ ዘላቂ አጋርነት እንዲገነቡም በፎረሙ ላይ ጥሪ ቀርቧል።
መረጃው በብራስልስ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
