EthiopiaNews

የብሔራዊ ባንክ ውሳኔ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በ26 ዋና ዋና ከተሞችና በሐረሪ ክልል የሚገኙ የሁሉም ባንክ ደንበኞች የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲያስተሳስሩ አሳስቧል፡፡

በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ ደንበኞች ደግሞ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንዲያጠናቅቁ የወሰነ ሲሆን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሂሳባቸውን የማያስተሳስሩ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸው ከወጪ ወይም ተቀናሽ ግብይት የታገደ እንደሚሆን ገልጿል፡፡

ነባር የባንክ ሂሳቦችን ከፋይዳ ቁጥር ጋር የማስተሳሰር ስራ ከታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ባንኮች ተግባራዊ መሆኑን ያስታወሰው ባንኩ ከአጠቃላዩ የባንክ ሂሳብ ባለቤቶች ቁጥር አንጻር ሲታይ ግን አፈጻጸሙ ዝቅተኛ ሆኖ መገኘቱን ጠቁሟል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv