EthiopiaNews

የተማሪዎች ምረቃ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በልዩ ልዩ የጤና ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 556 ተማሪዎችን በትናንትናው እለት አስመረቀ።

በምረቃው ስነስርዓት ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተመራቂዎች ለዚህ ስኬት በመብቃታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም ይህ ቀን ለእናንተ ብቻ ሳይሆን ለሀገርም ትልቅ የምስራች ነው ብለዋል።

ሚኒስትሯ ተመራቂዎች የህዝብን ጤና የመጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን ገልጸው፣ በሙያቸው ሀገራቸውን በታማኝነት እንዲያገለግሉ አደራ ብለዋል።

መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv