የትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የስራ ባልደረባ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው

ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታውቀው የመስሪያ ቤቱ  የስራ ባልደረባ የነበሩት አቶ ሙላት ጸጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህ ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት ነው ድንገት ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን ማጣታቸውን የገለጸው።

የሚኒስቴር መስሪያቤቱ በሁለቱ ግለሰቦች ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።