EthiopiaNews

የትራፊክ አደጋ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በመዲዋ በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታወቀ፡፡

ዛሬ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 11፡30 በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ኮተቤ 02 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አደጋው መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።

የጉዞ መነሻውን ከአንቆርጫ ወደ ላምበረት ያደረገው አንድ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ 18 ሰዎችን ጭኖ በተጠቀሰው ቦታ ቁልቁለቱን በመጓዝ ላይ ሳለ ባጋጠመው የመገልበጥ አደጋ 3 ሰዎች መሞታቸው እና 16 ሰዎች ላይ ደግሞ የከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የሚገኝ ሲሆን የአደጋው መንስኤም እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡

መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews