የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ማኒፌስቶ
የአራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ካሸነፈ አማርኛን ብሔራዊ ቋንቋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ጥምረቱ ይህን ያስታወቀው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፍበትን የምርጫ ማኒፌስቶ ባስተዋወቀበት ጊዜ ነው።
ኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ መኢአድና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ በጥምረት የመሰረቱት ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ እንደ ጥምረት በአንድ የምርጫ ምልክት እንደሚወዳደር መግለጹ ይታወሳል።
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በርካታ ፖለቲካዊ ምጣኔ ሃብታዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን ባካተተበት ማኒፌስቶው ለዜግነትና ለግለሰቦች መብቶች ቅድሚያ በሰጠ መልኩ የስርዓት ለውጥና የህገመንግስት ማሻሻያ እንደሚያደርግም ገልጿል።
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክርቤቶች 1054 እጩዎችን ማቅረቡን ከፓርቲው የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
