የትንሳኤ በዓልን ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት እንዲያከብር በቂ ዝግጅት መደረጉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በመላ ሀገሪቱ ህብረተሰቡ የትንሳኤ በዓልን ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት እንዲያከብር በቂ ዝግጅት መደረጉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።ኮሚሽኑ በበዓሉ ወቅት ከህዝቡ ጋር በመሆን ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር በርካታ የፀጥታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ነኝ ያለ ሲሆን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በንፁሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማስቆምም ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የህግ የበላይነትን የማስከበር ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።በዚህም በተለያዩ አካባቢዎች ታጥቀው ጥቃት እያደረሱ ያሉ አካላትን ለፍትህ ለማቅረብ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ መጪውን ሀገራዊ ምርጫም እንዲሁ ደህንነቱ የተረጋገጠ እንዲሆን በገለልተኝነት በማገልገል ላይ እገኛለሁ ብሏል፡፡ በሌላ በኩል ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና ሌሎች ታላላቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን በንቃት እየጠበኩ እገኛለሁ ሲል በማህበራዊ የትስስር ገጹ አሳውቋል፡፡በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኪሚሽንም መጪው የትንሳኤ በዓል በከተማዋ በሰላም ተከብሮ ያልፍ ዘንድ በቂ ዝግጅት ስለማድረጉና ለ6ኛው አገራዊ ምርጫም እንዲሁ የጸጥታ ችግር እንዳይከሰት ከወዲሁ ስራዎችን እየሰራ ስለመሆኑ አመልክቷል፡፡

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs