LatestNews

በመኪና አደጋ ህይወታቸው እያለፈ የነበሩ ፖሊሶችን በቪዲዮ ሲቀርጽ የነበረ አውስትራሊያዊ እስራት ተፈረደበት፡፡

በመኪና አደጋ ህይወታቸው እያለፈ የነበሩ ፖሊሶችን በቪዲዮ ሲቀርጽ የነበረ አውስትራሊያዊ እስራት ተፈረደበት፡፡ሪቻርድ ፓውሲ የተባለው ግለሰብ ባለፈው የፈረንጆች አመት የፖሊስ አባላቱን ሞት በቪዲዮ የቀረጸው በሜልቦርን አውራ ጎዳና እሱን ለማሰር በመኪና ሲያባርሩት የፖሊሶቹ መኪና በሌላ መስመሩን በሳተ ከባድ መኪና ከተገጨ በኋላ ነው፡፡በዚሁ ግጭት ሳቢያ አራቱም የፖሊስ አባላት ለሞት ሲያጣጥሩ ግለሰቡ ከመኪናው ወርዶ ቪዲዮ ይቀርጻቸው ነበር ተብሏል፡፡ በተለይም እርሱ በሞባይሉ ቪዲዮ ሲቀርጽ ከተገጨው መኪናው ስር የነበረች አንድ የፖሊስ አባል ትንሽ እርዳታ ቢያደርግላት በህይወት ትተርፍ ነበር ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ጉዳዩን ሲያይ የነበረው ፍርድ ቤት የፊልም ቀረጻውን ሀላፊነት የጎደለው ተግባር በሚል ተከሳሹ ላይ የ10 ወራት እስራት ፈርዶበታል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ግለሰቡ አሁን እስራት ቢፈረድበትም እስካሁን ከ3 መቶ ቀናት በላይ በእስር በመቆየቱ በቀናት እድሜ ቅጣቱን ጨርሶ ይፈታል፡፡ ሆኖም የሟቾቹ የፖሊስ አባላት ቤተሰቦች የእስራቱ መቅለል በእጅጉ አበሳጭቷቸዋል፡፡

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs