LatestNews

የገንዘብ ኖት ቅያሪ ተከትሎ 126 ቢሊዮን ብር ወደ ባንክ መግባቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

ከወራት በፊት አገራችን ያደረገችውን የገንዘብ ኖት ቅያሪ ተከትሎ በተከፈቱ አዳዲስ የባንክ ሒሳቦች አማካኝነት 126 ቢሊዮን ብር ወደ ባንክ መግባቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ አጠቃላይ ዋጋቸው ከ262 ቢሊዮን ብር በላይ የሆኑ አዳዲስ የብር ኖቶች መታተማቸውን ገልፀው፤ ከዚህ ውስጥ 185 ቢሊዮን ብር ለባንኮች መሰራጨቱን ተናግረዋል።ከብር ኖት ቅየራ ጋር በተያያዘ የወጡ መመሪያዎች ለፋይናንስ ተደራሽነቱ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም ዶክተር ይናገር የገለጹ ሲሆን ቅየራው ህግን ተከትለው ለሚሠሩ ዜጎች ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩ ባለፈ ለሁሉም የተመቸ ህጋዊ የግብይት ስርዓትን መዘርጋት ማስቻሉንም አመልክተዋል። በሌላ በኩል በትግራይ የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ በክልሉ የብር ኖት ቅየራውን ሂደት አስተጓጉሎ የነበረ ቢሆንም ቅየራው በስኬት ተጠናቋል ያሉት ዶ/ር ይናገር አዳዲሶቹ የብር ኖቶች ረዘም ላለ ጊዜ እንዲያገለግሉ ህብረተሰቡ በጥንቃቄ እንዲጠቀማቸው ጠይቀዋል።

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs