LatestNews

ዜጎች በ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቅርበዋል።

ዜጎች በ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቅርበዋል።በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲጎለብት የዜጎች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በተለይ በምርጫ ወቅት ዜጎች በልዩ ልዩ መንገዶች ተሳትፏቸውን ሊያረጋግጡ ይችላሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካርድ ወስደው በሰላማዊ መንገድ ለመምረጥ ራስን ከማዘጋጀት ባለፈ በሲቪክ ማኅበራት አማካኝነት የምርጫው ሂደት ግልጽና ተዓማኒ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ይጠበቃል ነው ያሉት።ለአብነትም ዜጎች በሲቪክ ማህበራት በኩል በምርጫ ካርድ አሰጣጡ ዙሪያ፣ የምርጫ ቅስቀሳን በተመለከተና የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ ቁጥጥር እንደሚያደርጉና ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን በቅድመና ድህረ ምርጫ ወቅት የሚያጋጥሙ ግጭቶችን ለማስቀረት የማይተካ ሚና እንዳላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs