EthiopiaNews

የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተባለ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ አሁን ባለበት እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ሚንስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልእክት የነዳጅ ማደያዎች ያልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ማሳሰቢያ መስጠታቸውን ከማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ተመልክተናል።